አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 370 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ተመላሾቹ 329 ወንዶች፣ 39 ሴቶችና 2 ጨቅላ ህጻናት ሲሆኑ ÷ ከእነዚህ መካከልም 16 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ የማድረግና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ስራ እስካሁን ከ86 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡