የሀገር ውስጥ ዜና

ለፌደራል ፖሊስ ጀግኖች ማዕከል የሞተር ሳይክል ድጋፍ ተደረገ

By amele Demisew

October 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ‘ሳንፖሎ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል’ አምራች ኩባንያ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጀግኖች ማዕከል ሞተር ሳይክሎችን በድጋፍ አበረከተ፡፡

ሞተር ሳይክሎቹ በማዕከሉ ሆነው ከጉዳታቸው እያገገሙ ለሚገኙ የፖሊስ አመራርና አባላት አገልግሎት እንደሚውሉ መገለጹን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

ድጋፉንም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጤና አገልግሎት ዋና መምሪያ መረከቡ ተገልጿል፡፡