Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኮርፖሬሽኑ ከቻይና ማኑፋክቸሪንግ እና ፈርኒቸር ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ኢንቨስትመንት በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የኤሌክትሪክ መኪኖችንና ዘመናዊ የቢሮ እቃዎችን ከሚያመርት የቻይና ኩባንያ ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

የውል ስምምነቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) እና የአንዳ ቨሂክል ማኑፋክቸሪንግ እና አንይ ፈርኒቸር ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስፈጻሚ ው ሃንግሹ ጋር ተፈራርመዋል፡፡

ኩባንያው በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ 2 ሄክታር የለማ መሬት ከኮርፖሬሽኑ በመረከብ ወደ ስራ የሚገባ ሲሆን÷ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባም ለበርካታ ዜጎች የስራ እድልን ይፈጥራል ነው የተባለው፡፡

በዚህም ኩባያው ምርቶቹን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ይሆናል መባሉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ከ140 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶቸ በተለያዩ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን÷ የቻይናውያን ባለሃብቶች ተሳትፎም ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል ፡፡

Exit mobile version