ስፓርት

የካፍ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

October 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በስብስባው ላይ የካፍ ፕሬዚዳንት እና የኮሚቴው ሰብሳቢ ፓትሪስ ሞትሴፔን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ እንዲሁም ጨምሮ ሌሎች የኮሚቴው አባላት ተገኝተዋል፡፡

በተመሳሳይ የሴካፋ አባል ሀገራት ውይይት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በስካይላይት ሆቴል ተካሂዷል፡፡

በሌላ በኩል 46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ጠቅላላ ጉባዔ ነገ በአዲስ አበባ እንደሚካድ መገለጹን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡