የሀገር ውስጥ ዜና

ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር እና ኢትዮ ቴሌኮም የስማርቲ ሲቲ ፕሮጀክት ትግበራ ስምምነት ተፈራረሙ

By Feven Bishaw

October 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር እና ኢትዮ ቴሌኮም የስማርቲ ሲቲ ፕሮጀክት ትግበራ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬ ሕይወት ታምሩ እና የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ናቸው፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ከተሞች እንደከተማነታቸው ለዜጎች እርካታን ማስገኘት የሚያስችሉ ተቋማት ሊኖራቸው ይገባል፡፡

በባሕር ዳር ከተማ የተጀመረው የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ውጤታማ እንዲሆንም ባለ ድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

አቶ ጎሹ በበኩላቸው÷ ባሕር ዳርን ምርጥ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ከተማ ለማድረግ የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት የስማርት ባሕር ዳር ጽሕፈት ቤት ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡

ከተሞች ነገን ታሳቢ አድርገው ዛሬ ላይ ዝግጁ እንዲሆኑ መጪውን ትውልድ ታሳቢ ያደረገ ታሪካዊ አመራር መስጠት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

በደሳለኝ ቢራራ