አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ) ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ እና ከካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዛሬ ጠዋት ተወያይተዋል፡፡
ይህን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ ዛሬ ጠዋት ኢትዮጵያ እያስተናገደች ከምትገኘው 46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መደበኛ ጉባኤ አስቀድሞ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔን እና የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከፍተኛ አመራሮችን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብያለሁ ብለዋል።
በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የአደይ አበባ ስታዲየምንም በጋራ መጎብኘታቸውን ገልጸዋል፡፡
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ይህ ጠቃሚ ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን ለማገዝ በሚገባ ተዘጋጅታለች ሲሉም በፅሁፋቸው አስፍረዋል።