አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ብለዋል፡፡
ዛሬ ማለዳ ዋና ፀሃፊውን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በተለያዩ ቀጣናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውንም ገልጸዋል፡፡