Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ብለዋል፡፡

ዛሬ ማለዳ ዋና ፀሃፊውን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በተለያዩ ቀጣናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውንም ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version