አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፊፋ ዋና ጸሃፊ ላርስ ኒልስ ማቲያስ ግራፍስትሮም እና የካፍ 3ኛው ም/ፕሬዚዳንት ሱሌማን ዋበሪ በ46ኛው የካፍ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ሁሪያ አሊ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ ነፊሳ አልመኻዲ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።