Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቶሮንቶ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳ ቶሮንቶ በተካሄደ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸንፈዋል፡፡
አትሌት ዋጋነሽ መካሻ በቶሮንቶ ሴቶች ማራቶን ርቀቱን 2 ሰዓት 20 ደቂቃ ከ44 ሰከንድ በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች፡፡
በተመሳሳይ በወንዶች ቶሮንቶ ማራቶን ውድድር አትሌት ሙሉጌታ አሰፋ አሸንፏል፡፡
አትሌት ሙሉጌታ ውድድሩን በ2 ሰዓት 7 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ በመግባት ነው ቀዳሚ መሆን የቻለው፡፡
Exit mobile version