አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሼህ ሞሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሩሲያ ሞስኮ ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ሞስኮ ቨኑኮቮ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በሩሲያ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ተገልጿል፡፡
በሞስኮ በሚኖራቸው ቆይታም ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ እንዲሁም የደኅንነት ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኤምሬትስ ኒውስ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
በተጨማሪም ከነገ በስቲያ በሩሲያ ካዛን ከተማ በሚካሄደው 16ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ ላይ እንደሚሳተፉ ዘገባው አመላክቷል፡፡