Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጫሞ ሐይቅ ከደረሰው የጀልባ መስጠም ጋር በተያያዘ እስከ አሁን 12 አስከሬን ተገኝቷል – ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአቡሎ አርፋጮ ወደ አርባምንጭ ከተማ 16 ሰዎችን እና ሙዝ ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ባሳለፍነው ሐሙስ 10 ሠዓት ከ20 ገደማ ጫሞ ሐይቅ ላይ መስጠሟ ይታወቃል፡፡

አደጋውን ተከትሎም እየተከናወነ ባለው የነፍስ አድን ሥራ ትናንት 2 ዛሬ ደግሞ 10 አስከሬን መገኘቱን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር ደበበ ኦንቶ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል፡፡

በሌላ በኬሉ እስከ ዓርብ ድረስ 3 ሰዎች በሕይወት መገኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ በጀልባ ከተሳፈሩት መካከል እስከ አሁን የአንዱ ሰው ሁኔታ ስላልታወቀ ፍለጋው ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

ስለ አደጋው መንስዔ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽም÷ “የጀልባዋ የመጫን አቅም 35 ኩንታል ሆኖ ሳለ በዕለቱ 70 ኩንታል ሙዝ እና 16 ሰዎችን ጭና ነበር፤ ይህም ከልክ በላይ መጫን በመሆኑ ለአደጋው መከሰት መንስዔ ሆኗል” ብለዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

Exit mobile version