ስፓርት

በአካል፣ በመንፈስ እና ሥነ-ልቦና ብቁ  ዜጋ ለማፍራት ያለመ ንቅናቄ ማስጀመሪያ ተካሄደ

By ዮሐንስ ደርበው

October 20, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአካል፣ በመንፈስ እና ሥነ-ልቦና ብቁ እንዲሁም ባለራዕይ ጀግና ዜጋ ለመገንባት ከፍተኛ ሚና እንዳለው የተነገረለት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በወዳጅነት ዐደባባይ ተካሂዷል፡፡

የንቅናቄውን ማስጀመሪያ ያዘጋጁት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እና ሄኖክ ኪዳነወልድ ስፖርት ስልጠናዎች በመተባበር  ነው ተብሏል፡፡

በዕለቱም ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ታዋቂ ሰዎች መገኘታቸውን ከአንድት ፓርክ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚሁ መሠረት በአካል፣ በመንፈስ እና ሥነ-ልቦና ብቁ እንዲሁም ባለራዕይ ጀግና ዜጋ ለመገንባት ንቅናቄው ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተነግሯል፡፡

ሳምንቱን ሙሉ ከማለዳው 12 ሠዓት ጀምሮ ክፍት የሆነው ወዳጅነት ዐደባባይ÷ ለማንኛውም አካላዊ እንቅስቃሴዎችና አዕምሯዊ እረፍት ተመራጭ ሥፍራ መሆኑም ተገልጿል፡፡