Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአምስተርዳም ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአምስተርዳም ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸንፈዋል፡፡

አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው በአምስተርዳም ሴቶች ማራቶን የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡

አትሌቷ ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ በማጠናቀቅ ነው የቦታውን ክብረወሰን ማሻሻል የቻለችው፡፡

በተመሳሳይ በወንዶች የአምስተርዳም ማራቶን ውድድር ጸጋዬ ጌታቸው ርቀቱን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ አሸንፏል፡፡

Exit mobile version