Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በእስራኤል ዜጎች ላይ ጉዳት የሚያደርስ የትኛውም አካል ከባድ ዋጋ ይከፍላል አሉ ጠ/ሚ ኔታንያሁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራኤል ዜጎች ላይ ጉዳት የሚያደርስ የትኛውም ወገን ከባድ ዋጋ ይከፍላል ሲሉ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አስጠነቀቁ፡፡

የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ ትናንት የጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁን መኖሪያ ቤት ዒላማ ያደረገ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንሁ እንዳሉት÷“የኢራን ተላላኪ የሆነው ሂዝቦላህ እኔን እና ባለቤቴን ለመግደል ያደረገው ሙከራ ከባድ ስህተት ነው፡፡”

ድርጊቱ እስራኤል ደህንነቷን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ጠላቶቿ ላይ የጀመረችውን ጦርነት አንድ እርምጃ እንደማያስቆመው አረጋግጠዋል፡፡

ኔታንያሁ በእስራኤል ዜጎች ላይ በየትኛውም ሁኔታ ጉዳት የሚያደርስ አካል ከባድ አጻፋዊ እርምጃ ይጠብቀዋል ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ጦር በጋዛ እና ቤሩት ላይ የሚፈጽመውን የአየር ጥቃት አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል፡፡

ጦሩ በዛሬው ዕለት በሰሜናዊ ጋዛ በፈጸመው ጥቃት 73 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን÷በርካቶች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ እስራኤል በደቡባዊ ቤሩት የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድንን ኢላማ ያደረገ የአየር ጥቃት መፈጸሟ ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version