Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የምህንድስናውን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ የዲጂታላይዜሽን ትግበራ ትልቅ ፋይዳ አለው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በምህንድስናው ዘርፍ ውጤታማ ስኬቶችን ለማስመዝገብ የዲጂታላይዜሽን ትግበራ ትልቅ ፋይዳ አለው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚገኘውን የልህቀት ዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን የሪፎርም ሥራዎች ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም ምቹ የሥራ ከባቢ ግንባታና የዲጂታላይዜሽን የሪፎርም ሥራዎች በምህንድስናው ዘርፍ ኮርፖሬሽኑን ወደ ተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ እንደሆኑ መመልከታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

Exit mobile version