Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመልካ ባሮ ኢሬቻ በዓል በጋምቤላ ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 ዓ.ም መልካ ባሮ ኢሬቻ በዓል በጋምቤላ ከተማ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉ አባገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች እንዲሁም ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

የበዓሉ ታዳሚዎች በባህላዊ አልባሳት ደምቀው ባህላዊ ጭፈራዎችንና ልዩ ልዩ ዜማዎችን በማዜም በዓሉን እያከበሩ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በሰላም በመጠናቀቁ ሁሉን ነገር ለፈጠረ አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበትና መጪው ዘመን መልካም እንዲሆን ፈጣሪን የሚለመንበት በዓል ነው፡፡

Exit mobile version