የሀገር ውስጥ ዜና

በግንባታ ላይ ባለው የመቄዶኒያ ህንጻ ስር ባለ መጋዘን ላይ የተከሰተ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ

By Mikias Ayele

October 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በግንባታ ላይ ባለው የመቄዶኒያ የአእምሮ ህሙማንና የአረጋዊያን መርጃ ህንጻ ስር ባለ መጋዘን ላይ ተከስቶ የነበረ እሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም በለሚኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 3 መቆዶኒያ የአእምሮ ህሙማንና የአረጋዊያን መርጃ ማህበር  እያስገነባ ባለዉ ህንጻ ስር ባለ መጋዘን ላይ እሳት አደጋ መከሰቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ በደረሰዉ ጥሪ መሰረት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቦታዉ ፈጥነዉ በመድረስ እሳቱ ሳይስፋፋ በፍጥነት መቆጣጠር ችለዋል።

በእሳት አደጋዉ በመጋዘን ውስጥ የነበሩ ልዩ ቁሳቁሶች ላይ መጠነኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን ተናግረዋል።