Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአባ መፍቀሬ ሰብዕ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐይማኖታዊ አስተምኅሮ፣ በብዝኃ ሕይወት ጥበቃ ሥራ እና አንድነትን በማስተማር ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አድባራት ያገለገሉት አባ መፍቀሬ ሰብዕ ኪዳነወልድ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ።

የአባ መፍቀሬ ሰብዕ አስክሬን ለዓመታት ካገለገሉበት የደሴ ከተማ ከተሸኘ በኋላ በሐይቅ እስጢፋኖስ እና አቡነ ኢየሱስ ሞአ አንድነት ገዳም ስርአተ ቀብራቸው ተፈፅሟል።

በ1921 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ተጉለት ወርቅጉር አካባቢ የተወለዱት አባ መፍቀሬ ሰብዕ በግሸን ደብረ ከርቤ ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ ቆይተው በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ባለፈው ማክሰኞ ማረፋቸው ይታወሳል።

Exit mobile version