Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፓን አፍሪካ ጠበቆች ማህበር አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓን አፍሪካ ጠበቆች ማህበር አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ጠበቆች ከጥቅምት 6 ጀምሮ ሲያካሂዱት የቆየውን 14ኛ ጉባዔያቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ነው በመታሰቢያው ጉብኝት ያደረጉት፡፡

አባላቱ ኢትዮጵያ በቅኝ ያልተገዛች ጠላቶቿን በተባበረ ክንድ ድል በማድረግ ለመላው አፍሪካውያን ነፃነት መሰረት የሆነውን የዓድዋ ድል ለመዘከር የተገነባውን መታሰቢያ በመጎብኘታቸው ኩራት እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

በታሪኩ ወልደሰንበት

Exit mobile version