የሀገር ውስጥ ዜና

የተቋምና የሲቪል ሰርቪስ ለውጥ ሥራዎች የእድገት ጥረታችንን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

By Mikias Ayele

October 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ስንተገብራቸው የቆየነው የተቋም እና የሲቪል ሰርቪስ ለውጥ ሥራዎች የእድገት ጥረታችንን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የመጀመሪያ ሩብ አመት የ100 ቀን ግምገማችን በተለያዩ ዘርፎች ላቅ ያሉ እድገቶች መመዝገባቸውን አሳይቶናል ብለዋል።

ይሁንና የእድገት አቅጣጫችን ከፊታችን የበለጠ ሥራ እንደሚቀረን ያመለክተናል በማለት ገልጸዋል።

ስንተገብራቸው የቆየነው የተቋም እና የሲቪል ሰርቪስ ለውጥ ሥራዎች የእድገት ጥረታችንን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ በማለት ገልጸው፤ የሕዝብ አገልግሎቱ ዘርፍ አዲሱን የማብቃት ባሕል እንዲያሳድግ እና ሌሎችም ውጤታማ እንዲሆኑ እንዲደግፍ እጠይቃለሁ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።