Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሽብርተኝነትን በመዋጋት የተገኘው ውጤት መቀልበስ የለበትም- ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትን በመዋጋት የተገኘው ውጤት መቀልበስ እንደሌለበት ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ አስገነዘቡ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ምክትል ዋና ጸሐፊ እና የፖለቲካ እና የሠላም ግንባታ ጉዳዮች ኃላፊ ሮዝመሪ ዲካርሎ ጋር መወያየታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ገልጸዋል፡፡

በውይይታቸውም በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች በተለይም በሶማሊያ ሰላም እና ፀጥታ ላይ መምከራቸውን ነው የገለጹት፡፡

በዚህም ሽብርተኝነትን በመዋጋት የተገኘው ውጤት መቀልበስ እንደሌለበት ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ርምጃ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

Exit mobile version