Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኃያል ሀገር ለልጆቻችንን ለማቆየት ያገኘነውን ዕድል እንጠቀማለን – ም/ጠ/ሚ ተመስገን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለንተናዊ ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠ አፍሪካዊት ልዕለ ኃያል ሀገር ለልጆቻችንን ለማቆየት ያገኘነውን መልካም ዕድል ሳናባክን እንጠቀማለን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ከትናንት ታሪካችን በጎዎችን እያደስንና እያስዋብን፤ ህፀፆችን እያረምንና እያስተካከልን በትናንትናው ብቻ ሳንታጠር ዛሬን በአገልጋይነት ስሜትና በታታሪነት በከፍተኛ የትጋት መንፈስ ጠንክረን በመስራት፤ የልፋትና ድካም ውጤታችን የሚንፀባረቅበት ያማረና የተዋበ ነጋችንን ለመጭው ትውልድ በማውረስ ታሪክ እንሰራለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ለዘመናት ጠፍሮ ከያዘን አዙሪት ተላቅቀን፤ ዕድሎቻችንን ሳናባክን፤ የገጠሙንን ችግሮች እየተጋፈጥን፤ በስኬቶቻችን ሳንዘናጋ ወደ ብልፅግናችን እንገሰግሳለን ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም ሁለንተናዊ ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠ አፍሪካዊት ልዕለ ኃያል ሀገር ለልጆቻችንን ለማቆየት ያገኘነውን መልካም ዕድል ሳናባክን እንጠቀማለን ብለዋል፡፡

Exit mobile version