አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በሶማሌላንድ ላይ የጦር ሰፈር ለመገንባት ፍላጎት እንዳላት የተለያ መገናኛ ብዙኃ እየዘገቡ ነው፡፡
የጦር ሰፈር ግንባታው የሃውቲ አማፂያን በቀይ ባህር የሚፈፀሙትን ጥቃት ለመከላከል፣ የባብ ኢል-ማንዳብ ስትሬት ደኅንነትን ለመጠበቅ እና በቀጣናው የሚፈፀሙ ወንጆሎቸን ለመከላከል ያለመ ነው ተብሏል፡፡
ለዚህም እስራኤል ለሶማሌላንድ እውቅና በመሥጠት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደምትፈጥር መገለጹን ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡
በምሥራቅ አፍሪካ ስትራቴጂክ ከሚባሉ አካባቢዎች አንዷ እንደሆነች የሚነገርላት ሶማሌላንድ÷ አንድ ሦስተኛው የዓለማችን የባሕር ንግድ ዝውውር እንደሚከናወንባት ዘገባው አመላክቷል፡፡
ሶማሌላንድ ከኤደን ባሕረ ሰላጤ በ740 ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝ ሲሆን የባብ ኢል-ማንዳብ መስመር እና ቀይ ባሕርን ደኅንነት÷ ከሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የባሕር ላይ ውንብድናና ሌሎች የሽብር ጥቃቶች ለመካለከል ቁልፍ ቦታ መሆኗ ይነገራል፡፡