ስፓርት

የፕሪሚየር ሊጉ 4ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከነገ ጀምሮ ይቀጥላል

By ዮሐንስ ደርበው

October 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከእረፍት መልስ ከነገ ጀምሮ በድሬዳዋ ስታዲየም በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላል፡፡

በዚሁ መሠረት ነገ 10 ሠዓት ላይ ሀዲያ ሆሳዕና ከሐዋሳ ከተማ እና ምሽት 1 ሠዓት ላይ መቐለ 70 እንደርታ ከመቻል የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

እንዲሁም ከነገ በስቲያ 10 ሠዓት ላይ ስሑል ሽረ ከድሬዳዋ ከተማ ሲጫወቱ በዚሁ ዕለት ምሽት 1 ሠዓት ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር ይፋለማሉ፡፡

የ4ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ሲቀጥል የፊታችን ሰኞ ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም አዳማ ከተማ ከፋሲል ከነማ ይጫወታሉ፡፡

ማክሰኞ ዕለት ደግሞ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከባሕር ዳር ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ከሲዳማ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡