የሀገር ውስጥ ዜና

የምክር ቤት አባላት የሀገር ህልም እንዲሳካ ለማስቻል ከፍተኛ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል-አቶ አደም ፋራህ

By amele Demisew

October 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ ህልም እንዲሳካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለፁ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት ÷የምክር ቤት አባላት ካለባቸው ሕዝባዊ ኃላፊነት አኳያ የሀገር ህልም እንዲሳካ ከፍተኛ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እንዲሠሩ ያስፈልጋል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያ ወደ ተሻለ ከፍታ የሚያደርሳትን እና ለትውልድ የሚሻገር ህልም ተልማለች፤ ይህ ህልም እውን ይሆን ዘንድም ምቹ ነባራዊ ሁኔታዎች አሏት ማለታቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

“ሀገሪቱ ያላት እምቅ የተፈጥሮ ሀብት፣ ከዓላማው ጎን የሚሰለፍ ሕዝብ እንዲሁም የተገነቡ ተቋማት የሀገራችንን ህልም ዕውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች ከሚባሉት ውስጥ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው” ብለዋል፡፡