Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የደቡብ ኮሪያ ተማሪዎች በብርሀን የዐይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ዝግጅት አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደቡብ ኮሪያ የዐይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት የመጡ ተማሪዎች በብርሀን የዐይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ዝግጅት አቀረቡ።

የሙዚቃ ዝግጅቱ በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

ዝግጅቱ የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሩያ ረጅም ዘመናት የቆየ ወዳጅነትን እንደሚያጠናክር ተነግሯል።

የብርሀን የአይነስውራን አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርት ወይዘሮ አለም ከበደ እንደገለጹት፤ በሙዚቃ ቡድኑ የቀረቡት ዜማዎች በሁለቱ የባህል ልምድ ልውውጥ እንዲኖር ያስችላል።

በአዳሪ ትምህርት ቤቱ የሚገኙ ዐይነ ስውራን ተማሪዎች የሙዚቃ ተሰጥአቸውን እንዲያሳድጉ የሚያስችል ዝግጅት መካሄዱንም ተናግረዋል።

በአዲሱ ስርአተ ትምህርት ለሙዚቃም ሆነ አጠቃላይ የኪነ ጥበብ ዘርፍ በተሰጠ ትኩረት ትምህርቱ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መምህርቷ፤ የዛሬው ዝግጅት ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን በተግባር እንዲተረጉሙ እድል ፈጥሯል ብለዋል።

ዝግጅቱን ላቀረቡ የሙዚቃ ቡድኑ አባላት እና ዝግጅቱ እንዲካሄድ ላደረገው የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ምስጋና ማቅረባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መረጃ አመልክቷል።

 

Exit mobile version