Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከ2 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን መተካት መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአንድ ዓመት ብቻ ከውጭ የሚገቡ ከ2 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውንም ገልጸዋል።

ዘርፉ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ተጨባጭ አስተዋፅኦ ወደማበርከት እየተሸጋገረ ነው በማለት ገልጸው፥ በዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራም ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል።

የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ማሳደግ፣ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ሀገራዊ ወጪን መቀነስ ላይም ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።

ንቅናቄው ባለፈው ዓመት ብቻ ከ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ማስቻሉን መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

 

Exit mobile version