አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ የሃማስ ፖለቲካ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ሆኖ እያገለገለ የሚገኘው ያህያ ሲንዋር ሳይገደል እንዳልቀረ እስራኤል ገለጸች፡፡
የእስራኤል መከላከያ ሃይል÷ በጋዛ ሶስት የሀማስ ወታደሮችን መግደሉን የገለፀ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ የሀማስ የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ የሆነው ያህያ ሲንዋር ሊሆኑ እንደሚችል አስታውቋል።
ሲንዋር ለሃማስ እና ለኢስላሚክ ጂሃድ ኦፕሬሽን መሰብሰቢያ ሆኖ ያገለግል በነበረው ህንፃ ላይ በተወሰደ ጥቃት መገደሉን የገለፀው የእስራኤል መከላከያ ሃይል፤ በህንፃው ላይ የሚኖሩ ንፁሃን ዜጎች አልነበሩም ብሏል፡፡
የሃማስ ባለስልጣናት በበኩላቸው እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ ጃባሊያ በተባለው አካባቢ በፈፀመችው ጥቃት 22 ንጹሃን ተገድለዋል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡