Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፌዴራል ፖሊስ ወንጀልን በብቃት መከላከል የሚያስችል ጠንካራ ተቋም መገንባቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ወንጀልን በብቃት መከላከል የሚያስችል ጠንካራ ተቋም ገንብቷል ሲሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ፡፡

“አፍሪካ በጠንካራ አንድነት፣ ለሁለንተናዊ ፀጥታና ሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪካ ሀገራት መከላከያ ሚኒስትሮች ጉባዔ ተሳታፊዎች የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል÷ ተቋሙ ከተለያዩ ሀገራት ተሞክሮዎችን በመውሰድና በቅንጅት በመስራት ማሻሻያዎችን ማድረጉን ተናግረዋል።

በዚህም ከሀገር አልፎ ጠንካራ የሆነ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋም ለመገንባት ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቁመው÷ በተለይ በቴክኖሎጂ ለታገዝ የወንጀል ምርመራና መከላከል ስራዎች ትኩረት መሰጠቱን አንስተዋል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ

Exit mobile version