ስፓርት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል

By ዮሐንስ ደርበው

October 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጊኒ ጋር የነበረበትን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በሽንፈት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ከጊኒ አቻው ጋር ያደረጋቸውን ጨዋታቸው በደርሶ መልስ 7 ለ 1 መሸነፉ ይታወቃል፡፡

በነገው ዕለትም ቡድኑ ከጊኒ ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ እንደሚሰጥ መገለጹን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡