Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቢሾፍቱ የኮሪደር ልማትን ለማፋጠን የሚያስፈልጉ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ የኮሪደር ልማት ሥራን ይበልጥ ለማፋጠን የሚያስፈልጉ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ዛሬ ማለዳ የቢሾፍቱ የኮሪደር ልማት ሥራ ያለበትን ደረጃ ከከተማው አመራሮች ጋር በመሆን ገምግመናል ብለዋል፡፡

የተጀመረውን ይበልጥ ለማፋጠን የሚያስፈልጉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቢሾፍቱ ከተማ የኮሪደር ልማት የሥራ እንቅስቃሴን እንዲደግፉና እንዲከታተሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሥራ መመሪያ የተሰጣቸው መሆኑ ይታወቃል።

በቢሾፍቱ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ በአምስት አካባቢዎች ሰፊ በሆነ ቦታ ላይ የሚከናወን ሲሆን፤ በውስጡም የመንገድ፣ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገድ፣ የህዝብ መዝናኛ ፓርክ እንዲሁም መንገዶችን የማስዋብ ሥራዎችን አካቷል።

Exit mobile version