አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ነዣ አላዊ ማህሃምዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ እና በሞሮኮ መካከል ያለው ትብብር እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ማካሄድ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
ሁለቱም ወገኖች የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡