የሀገር ውስጥ ዜና

በሶማሌ ክልል የማህበረሰብ ወኪሎች የአጀንዳ ልየታ ምክክር መድረክ ተጠናቀቀ

By Melaku Gedif

October 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በሶስት ማዕከላት የተካሄደው የማህበረሰብ ወኪሎች የአጀንዳ ልየታ የምክክር መድረክ መጠናቀቁን የኢትዮጵ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የማህበረሰብ ክፍል ወኪሎች በ3 ማዕከላት ከወከሉት ማህበረሰብ ያመጧቸውን አጀንዳዎች አደራጅተው አጀንዳዎችን በአደራ ተረክበው ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የሚመካከሩ ወኪሎችን መምረጣቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመልክቷል፡፡