የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አደም ፋራህ በጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

By ዮሐንስ ደርበው

October 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር በነበሩት ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡

አቶ አደም ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክት÷ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡