የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

By Melaku Gedif

October 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር በነበሩት ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ መልዕክት÷ለሟች ቤተሰቦች፣ ሥራ ባልደረቦች እና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ባጋጠማቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።