አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢራን አየር መንገድ ወደ አውሮፓ ሀገራት መዳረሻዎች የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን አስታወቀ፡፡
ውሳኔው የአውሮፓ ህብረት ኢራን ኤር፣ ሳሃ ኤርላይን እና ማሃን ኤር በተባሉ የኢራን አየር መንገዶች ላይ የጣለውን ማዕቀብ ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
ወደ አውሮፓ መዳረሻዎች ለመሄድ ቲኬት ቆርጠው ለነበሩ መንገዶኞች በረራው ላልተወሰነ ጊዜ መቋረጡ በጽሁፍ መልዕክት እንዲያውቁ መደረጉ ተመላክቷል፡፡
የአውሮፓ ህብረት በሶስት አየር መንገዶች ላይ ለሩሲያ ሚሳኤልና ድሮን ሲያቀርቡ ነበር በሚል አዲስ ማዕቀብ መጣሉ ይታወሳል።
ህብረቱ ከአየር መንገዶቹ በተጨማሪ በሌሎች አራት ድርጅቶች እና ሰባት ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ መጣሉን ፕሬስ ቲቪ ዘግቧል።