አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች ፈጥነን በመሻገር ሁለንተናዊ ልማታችንን ማፋጠን ላይ በትኩረት መረባረብ ይገባናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስገነዘቡ፡፡
አቶ ተመስገን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ አብሮነት፣ አዲስ ሐሳብ እና ብሩህ ተስፋ ለብልፅግናችን ቁልፍ መሰረቶች ናቸው ብለዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ ዕይታችን ብርሃን፣ ገቢራችን እውነትና ዕውቀት፣ መዳረሻችን ደግሞ ሁለንተናዊ ብልፅግና ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡