Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትሮች የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሀገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች በቢሾፍቱ የሚገኘውን የኢትዮጵያ አየር ሃይል ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) ተገኝተዋል።

ለሶስት ቀናት የሚቆየው የአፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትሮች ጉባዔ በአዲስአበባ እየተካሄደ ሲሆን÷ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን በያዘው ውሎ የጉባዔው ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በዚህም በአየር ሃይል ቅጥር ጊቢ የሚገኙትን የበረራ ትምህርት ቤት፣ ኤር ቤዝን፣ የሲሙሌተር ማዕከልን እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን እንደጎበኙ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version