Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በባሕር ዳር በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 3 ሺህ ሊትር ነዳጅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሕር ዳር ዳር ከተማ ግሽ አባይ ክፍለ ከተማ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 3 ሺህ ሊትር ነዳጅ ተያዘ፡፡

ነዳጁ በሕገ-ወጥ መንገድ ከማደያዎች በሌሊት ተቀድቶ ሲወጣ በተደረገ ክትትል ከነተጠርጣሪዎቹ እጅ ከፍንጅ መያዙን የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት አስታውቋል።

10 በርሚል እና ከ50 በላይ ባለሁለት ሊትር ቤንዚን በክትትል ከተጠርጣሪዎቹ እጅ እንደተገኘም የከተማዋ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል፡፡

Exit mobile version