Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቶማስ ቱኸል የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመናዊው አሰልጣኝ ቶማስ ቱኸል የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ተሾመዋል፡፡

የቀድሞ የባየርን ሙኒክ እና ቼልሲ አሰልጣኝ የእንግሊዝ ሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን እስከ ፈረንጆቹ 2026 የሚያቆያቸውን ኮንትራት ለመፈረም ከእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ጋር መስማማታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ስምምነቱን ተከትሎም ከስዊድናዊው ሰቨን ጎራን ኤሪክሰን እና ከጣልያናዊው ፋቢዮ ካፔሎ በመቀጠል 3ኛው የእንግሊዝ ዜግነት ሳይኖረው የሀገሪቱ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ መሆን ችሏል፡፡

አሰልጣኝ ቶማስ ቱኸል የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድንን ለ2026ቱ ዓለም ዋንጫ ማዘጋጀት ቀዳሚ ሃላፊነታቸው ይሆናል ተብሏል፡፡

Exit mobile version