Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በ32 ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ከ828 ቢሊየን ብር በላይ ዝውውር ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች በተከናወኑ ግብይቶች 828 ቢሊየን 549 ሚሊየን 614 ሺህ 770 ብር ዝውውር መፈጸሙ ተገለፀ፡፡

ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥም በባንኩ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ከ145 ሚሊየን በላይ ግብይቶች መፈጸማቸውን የባንኩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በባንኩ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ከተፈፀመው ግብይት ውስጥ 84 በመቶ ያህሉ በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት መከናወኑም ተገልጿል፡፡

በገንዘብ ሲለካም ከ696 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ያህሉ በሞባይል ባንኪንግ የተፈጸመ ግብይት ነው ተብሏል፡፡

Exit mobile version