Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የከተማ ግብርና በኢትዮጵያ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ግብርና በኢትዮጵያ ተጠናክሮ እየተሠራ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከተሞች በግቢ ውስጥ በጥቅም ላይ ያልዋሉ ስፍራዎችን የምግብ ዋስትናን ወደ ሚያሳድጉ፣ ዘላቂነትን እና የኢኮኖሚ እድገትን ወደ ሚያመጡ አረንጓዴ ስፍራነት እየተቀየሩ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በዚህ አይነቱ ጠቃሚ ተግባር ለመሰማራትም በቀላሉ መጀመር እንደሚቻል ጽሕፈት ቤቱ መክሯል፡፡

ለአብነትም አነስተኛም ሆነ ትላልቅ ኮንቴይነሮችን፣ እንደቆጥ ሊያገለግሉ የሚችሉ ርብራቦችን በመጠቀም፤ ከጎረቤቶች ጋር በመቧደን፣ ዕውቀት፣ የሥራ ቁሳቁሶችን በመዋዋስ ዛሬውኑ መጀመር ይችላሉ ብሏል።

በሂደቱ ጠንካራ ጉርብትና እና ማኅበረሰብ ከመፍጠር ባሻገር÷ ትኩስ ምርት ከጓሮ ማግኘት የሚቻልበት ሁኔታ መኖሩንም አስገንዝቧል፡፡

Exit mobile version