የሀገር ውስጥ ዜና

ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን በወላይታ ዞን በኩታገጠም የለማ የጤፍ ሰብልን ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

October 15, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ በኩታገጠም የለማ የጤፍ ሰብልን ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸውም በወረዳው ሾጮራ ኦጎዳማ ቀበሌ በ157 ሔክታር መሬት ላይ በመኸር ወቅት በኩታገጠም የለማ የጤፍ ሰብልን ተመልክተዋል፡፡

በቀበሌው እየለማ በሚመገኘው የጤፍ ሰብል 242 አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን የርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

እየለማ ከሚገኘው የጤፍ ሰብልም 2 ሺህ 355 ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ በ”ዳኜ ዳባ የአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ ድርጅት” የፍራፍሬ ልማትን ጎብኝተዋል፡፡