Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂና ሰው ሰራሽ አስተውሎት መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ጨምሮ 180 ሀገራትን ያሳተፈው የዓለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ሁነት (ጂአይቴክስ ግሎባል 2024) በዱባይ እየተካሄደ ነው።

በዱባይ ዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል የተከፈተው ‘ጂአይቴክስ 2024’ በዓለም ለ4ኛ ጊዜ በሚካሄደው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሁነት ከ180 በላይ ሀገራት የተውጣጡ መሪዎች፣ የቴክኖሎጂ አልሚዎች፣ ስታርአፖች እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እየተሳተፉ ነው።

200 ሺህ ተሳታፊዎችን ባሰባሰበው በዚህ ግዙፍ መድረክ የጎንዮሽ ውይይቶች እየተደረጉ እንደሚገኙም ተመላክቷል፡፡

በመድረኩ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) እየተሳተፉ ነው።

በሌላ በኩል አራት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድጋፍ የራሳቸውን ምርትና አገልግሎት እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

Exit mobile version