አዲስ አበባ፣ ጥቅምት4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሶማሌ ክልል በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል፡፡
ቀኑ “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተከበረው፡፡
በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የፌደራል ፖሊስ አባላትና የመንግስት ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡