አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አባቶቻችን በመስዋዕትነት ያቆዩትን ሀገር ለሰንደቅ ዓላማ ተገቢውን ክብር በመስጠት ማስጠበቅ ይገባል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ተናገሩ፡፡
ቀኑ “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድሩ በተገኙበት በቦንጋ ከተማ ተከብሯል።
በዚህ ወቅት የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወንድሙ ኩርታ÷ ቀኑ የሀገራችንን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ቃላችን የምናድስበት ነው ብለዋል።
ሀገሪቱ ሁለንተናዊ ለውጥ እንድታረጋግጥ ለሰንደቅ ዓላማው ተገቢውን ክብር መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡
ሰንደቅ ዓላማችን የአንድነትና የነጻነት አርማ ነው ያሉት ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ርኢ/ር)፤ አባቶቻችን በመስዕዋትነት ያቆዩትን ሀገር ለሰንደቅ አላማ ተገቢውን ክብር በመስጠት ማስጠበቅ እንደሚገባ መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡