Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ከማክበር ባለፈ ብሔራዊ አንድነትን ለማጽናት መሥራት እንደሚገባ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችን እና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በአማራ ክልል ተከብሯል።

የሰንደቅ ዓላማ ቀን በአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች ነው የተከበረው።

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ በዚህ ወቅት÷ ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያውያን የነጻነታችን ምልክት፣ የአርበኝነት ምሰሶ፣ የብዝኃነታችን ማስተሳሰሪያ ገመድ ነው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ከማክበር ባለፈ ብሔራዊ መግባባትን ለማጠናከር እና ብሔራዊ አንድነትን ለማጽናት መሥራት ይገባልም ነው ያሉት አፈጉባኤዋ፡፡

ይህንን የነጻነት ምልክት የሆነ አርማ የሚገባውን ክብር መስጠት እና ማክበር የዚህ ትውልድ ኃላፊነት እና ግዴታ ሊሆን ይገባልም ብለዋል።

Exit mobile version