አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ቺካጎ በተካሄደው “ቺካጎ ማራቶን 2024 “የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡
በወንዶች ማራቶን ውድድር ኬንያዊው አትሌት ጆን ኬሪ 2 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ42 ሴኮንድ በመግባት በ1ኛነት ሲያጠናቅቅ ኢትዮጵያዊው መሐመድ ኢሳ ደግሞ በ2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ39 ሴኮንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል፡፡
በዚሁ ውድድር ኬንያዊው ሃሞስ ኪፕሩቶ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ5 ሴኮንድ በመጨረስ 3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡
በተመሳሳይ በቺካጎ ማራቶን 2024 በተካሄደው የሴቶች ሩጫ ውድድር ኬንያዊቷ አትሌት ሩት ቼፕንጊች በ2 ስዓት ከ9 ደቂቃ ከ57 ሴኮንድ በመግባት የአለም የማራቶን ሪከርድ የሰበረች ሲሆን÷ በዚሁ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ሱቱሜ ከበደ በ2 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ በመጨረስ 2ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡
ኬንያዊቷ አይሪኒ ቼፕታይ ደግሞ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ በማጠናቀቅ 3ኛ ደረጃን መያዝ ችላለች፡፡