የሀገር ውስጥ ዜና

ም/ ጠ/ ሚ ተመሥገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቢሮ እድሣትና የለውጥ ሥራዎችን ጎበኙ

By Feven Bishaw

October 13, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቢሮ እድሣት እና የለውጥ ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለዳኝነት ሥርዓቱ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል የሚደረጉ የለውጥ ሥራዎችን በተመለከተ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አለምአንተ አግደው ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

በጉብኝቱ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ÷ፍርድ ቤቱ የጀመረውን የትራንስፎርሜሽን የውጥ ሥራ እና በአዲሱ አመራር በአጭር ጊዜ የተመዘገበውን ጅምር ውጤት ማድነቃቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

የክልሉ መንግሥትም አስፈላጊዉን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በጉብኝቱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።